Tender Detail

Tender Details


በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን ሎት-1 የሠራተኞች ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት-3 ልዩ ልዩ ህትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት-4 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት -5 የመገልገያ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት 6 በህንፃና በቁሳቁስ ላይ የሚገ

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የካ አባዶ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ 02/2018 ዓ.ም

 

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን ሎት-1 የሠራተኞች ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት-3 ልዩ ልዩ ህትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት-4 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት -5 የመገልገያ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2,000፣ ሎት 6 በህንፃና በቁሳቁስ ላይ የሚገጠሙ የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000፣ ሎት7 የህክምና ቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 በ2018 የበጀት ዓመት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች:-

•        በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

•        የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡

•        የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፕሪንት አውት /ኮፒ/ ማቅረብ የሚችል

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

•        የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት /TIN/ ያላቸው

•        ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ ማቅረብ ሲኖርባቸው ደምሮ ሲፒኦ ማስገባት አይቻልም። በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ / እንዲሁም አሸናፊ ከሆኑ የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባችሁ፡፡

•        ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡

•        ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ (ለየሎት) የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 403 መውሰድ ይችላሉ፡፡

•        ሳምፕል የሚያቀርቡ ተጫራቾች አሸንፈው በሚገቡ ጊዜ በዋጋ ልዩነት በሚል ሰበብ አይነት እና ይዘታቸው የተለወጠ እቃ ማቅረብ አይችሉም፤

•        ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የተደረገ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ዶክመንት ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱ ማህተም ተመቶ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

•        ይህ ጨረታ በአዲሰ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከረዳት ፋይናንስ ቢሮ በመግዛትና በመውሰድ በጨረታ ሰነዱ ላይ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ ዋጋ በማድረግ ሞልታችሁ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡

•        እቃ ሲያስገቡ ከ11፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት አለቦት፡፡ ክፍያ የሚፈፀመው እቃውን ጤና ጣቢያ አምጥታችሁ በባለሙያ ተፈትሾ ማሟላት የሚገባዉን ሁሉ አሟልቶ ሲገኝ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 0118-93-12-17

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ የካ አባዶ ኮንዶሚኒም ግቢ ውስጥ G-7 ብሎክ 306 ጀርባ አካባቢ

 

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender