Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenue Bureau Arada Branch Office) - 002/2018

ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ፡-

ሎት 1፡- ደንብ ልብስ

ሎት 2፡- የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት 3፡- ህትመት

ሎት 4፡- የተሽከርካሪ መኪና ጌጣጌጥ ቅባቶች እና ጎማ

ሎት 5፡- የታሸገ ውሃ

ሎት 6፡- የታሸገ ቆሎ

ሎት 7፡- የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች

ሎት 8፡- የጀነሬተር ጥገና

ሎት 9፡- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ጥገና ዕቃዎች ጨምሮ፤ ፎቶኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር ለጥገና አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች

ሎት 10 ፡ ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና አገልግሎት

በ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤

2.     የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /TIN/ ያላቸው መሆኑን፤

3.     በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር (online) የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ/ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል።

5.     የዕቃዎችን ዝርዝር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ለተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤

6.     ከሎት አንድ እስከ ሰባት ድረስ የምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 2 ሲሆን “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ናሙና /ሳምፕል/ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ ሎት ስምንት እስከ ሎት አስር ለምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 4 ቴክኒካል ሰነድ ”አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ "በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ሎት የፋይናንሻል የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ” በድምሩ ሁለት ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የድርጅቱ ስም ፣አድራሻ እና ማህተም የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት በየሎቱ በመፃፍ በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎኘ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ሱማሌ ተራ ባድረግ ህንፃ በአራዳ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

7.     ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 88 ቀን የሚቆይ ይሆናል።

8.     ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው የብር መጠን ሰንጠረዥ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን

1

ደንብ ልብስ

7,051.8

2

የጽህፈት መሳሪያዎች እና የአላቂ የቢሮ እቃዎች

5,733.5

3

ህትመት

13,150

4

የተሽከርካሪ መኪና ጌጣጌጥ ቅባቶች እና ጎማ

3,828.86

5

የታሸገ ውሃ

21,054

6

የታሸገ ቆሎ እና ኩኪስ

10,780

7

የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች

6,070

8

የጀነሬተር ጥገና

6,483.4

9

የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር ለጥገና አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች

10,000

10

ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና አገልግሎት

1,456.23

 

 

10. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።

11. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ /ቫት/ በፊት መሆኑን ገልፀው መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል።

13. የጥቃቀንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ከአደራጀው መስሪያ ቤት የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።

14. አሸናፊ ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀነስ ይችላል።

15. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ለተጫረተበት ዕቃ ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ከጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስረከብ ይኖርበታል፤

16. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

17. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-126-52-95 ወይም 011-126-55-17 መጠየቅ ይቻላል።

 

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender