Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የቋሚ እና የአላቂ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ


የቋሚ እና የአላቂ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የቋሚ እና የአላቂ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይፈልጋል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO /ሲፒኦ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።

4.     የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ቋሚ እና አላቂ ዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት ኦርጅናል እና ኮፒውን የፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።

7.     ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አላቂ ዕቃዎች ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0931561347/0913304979 ደውለው መጠየቅ ይችላል። በደ/ኢ/ክ/መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ

Save Tender