የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
መስፈርቶቹም፡-
1. ከ9 እስከ 10 ከፍል ወይም ከ150 እስከ 200 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሆኖ ቢያንስ እያንዳንዱ ክፍል ከ3×4m2 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከዚህ ውስጥ ሁለት ክፍል ከ5X7 m2 በላይ የሆነ፣
2. ቤቱ ውሃ፣ መብራት እና መፀዳጃ ቤት ኖሮት ሕንጻ ከሆነ መነሻ G+0 ሆኖ መጨረሻው ከG+2 በላይ ያልሆነ፣
3. ይህን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች ከሚዛን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ኳስ ሜዳ አጥር ድረስና ከሚዛን አደባባይ እስከ ቤርገስ ብልፅግና ጽ/ቤት እንዲሁም ከአደባባይ እስከ ጭስ ዓባይ ሆቴል ድረስ ሆኖ ከዋና አስፓልቱ በግራ እና ቀኝ እስከ 150ሜ ገባ ብሎ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፣
• ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆናችሁ የቫት ሰርተፊኬቱ ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን የምትሰጡት ዋጋ ቫት ማካተትና ያለማካተት በግልጽ መግለጽ ያለባችሁ ሆኖ ይህ ሳይገለጽ ከቀረ ያቀረባችሁት ዋጋ ቫት ያከተተ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
• ተወዳዳሪዎች ቤቱ ሕጋዊ ስለመሆኑ ወቅታዊ ግብር የከፈሉበት ሕጋዊ ደረሰኝ እና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፣
• ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ሚዛን አማን ቅርንጫፍ ቀርበው በመግዛት የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
• ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛ የስራ ቀን ከሰዓት በ8፡00 ተዘግተው በዚያ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
• ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ስልክ፡- +251-47-135-00-32/0917-82-86-19
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሚዛን አማን ቅ/ጽ/ቤት
