Tender Detail

Tender Details


የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከሕጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 06/2018

 

የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከሕጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎችም፡-

1.     ሶዴም ሃይፖ ክሎራይት 10%

2.     ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ

3.     ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ

4.     የውሃ ፍሳሽ ማመላከቻ /ጠቋሚ መሳሪያ /water leakage detecter/

5.     ሰርፌስ ፓምፕ

6.     ብትን ጨርቅ

7.     የተሰፉ ልብሶች

8.     የወንድና ሴት ጫማ

9.     ልብስ ስፌት

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።

1.     በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ

2.     በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

3.     ከጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረከት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፣

4.     ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽንና ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።

6.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ውሃ/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም።

7.     በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡00 ይከፈታል። 16ኛው ቀን እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8.     ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ ይሸፍንም።

9.     ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ከላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል፡፡

10. ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587716840፣ 0587711058፣ 0587711520

ማሳሰቢያ

1.     ኬሚካሉ በየወሩ ተከፋፍሎ በዓመቱ ውስጥ የሚመጣ መሆኑ ይታወቅ

2.     የቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎች እና ብትን ጨርቅ ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የዕቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፤ የዕቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የዕቃውን ዓይነት እንጂ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጥታችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን፤

3.     ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

 

የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender