የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ለማሟላት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልፅ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Amhara Region Police College (የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ)
ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ብግጨO1/2018
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ለማሟላት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልፅ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
ቁጥር 1 የቢሮ ፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ቁጥር 2 የጽህፈት መሳሪያ
ቁጥር 3 የጽዳት እቃ
ቁጥር 4 የተሽከርካሪ ጎማ
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፡-
1. የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ /TIN ማቅረብ/ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3. በጨረታው ለመሳተፍ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታውን ሰነድ ደብረ-ማርቆስ ከተማ በአዲሱ ግቢ አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል እስከ 15ኛው ቀን ድረስ መግዛት አለባቸው፡፡
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ስፍራ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የተወዳዳሪዎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግድም፡፡
7. የእቃዎችን ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0587714207
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ
