Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎች ዝርዝር

•        ሎት-1 የፅዳት እቃዎች

•        ሎት-2 የደንብ ልብስ

•        ሎት-3 ቋሚ እቃዎች

•        ሎት-4 የትራንስፖርት አገልግሎት

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት

በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው በግልፅ ጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

1.     ተጫራቾች በንግድ ምዝገባ የተመዘገቡና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.     ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል በእቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ (2) ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ሎት-1 የፅዳት እቃዎች - 10,000

ሎት-2 የደንብ ልብስ - 7,000

ሎት-3 ቋሚ እቃዎች - 20,000

ሎት-4 የትራንስፖርት አገልግሎት - 5,000

3.     ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ወረድ ብሎ ከውሃ ልማት ጎን በሚገኘው ወረዳ 5 ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ (200.00) ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

5.     ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

6.     ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

7.     የጨረታው መክፈቻ ቀን በ11ኛው ቀን ሆኖ ነገር ግን ከኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ጨረታ ይከፈታል፡፡

8.     የጨረታው አሸናፊ ጽ/ቤቱ ባቀረበው መጠን ወይም ብዛት እቃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

9.     የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ አምራች የሆነ ብቻ ሲሆን አምራች መሆኑና የሚያመርተው እቃ ተጠቅሶ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።

10. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ሞዴል መሠረት ብቻ ነው።

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

12. ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርበው እቃ (ናሙና ላይ የተለየ ምልከት ወይም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የተከለከለ ነው) አድርጎ ቢገኝ ከውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን። ማንኛውም ተጫራች ማህተሙን የሚጠቀሙት በወረቀት ላይ ማህተም በማድረግ ዕቃ ላይበፕላስተር በመለጠፍ ብቻ ነው።

13. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም እና የሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

14. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበት እቃ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርትና ሠራተኛ በማውረድና በማጓጓዝ ባቀረበው ናሙና መሠረት በ10 ተከታታይየሥራ ቀናት ውስጥ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

15. ለሚገቡ የቋሚ እቃዎች ለአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

16. ሰነዱን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡

17. ስርዝ ድልዝ ሰነድ ተቀባይነት የለውም እንዲሁም ለአንድ እቃ ከአንድ ዋጋ በላይ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡

18. ዋጋ ተወደደብኝ እቃው ጠፋኝ ማለት የማይቻል መሆኑ መታወቅ ያለበት መሆኑና ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ወረድ ብሎ ውሃ ልማት አጠገብ የወረዳው ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913382003/0923286082/0923481386

 

በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender