በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህከልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በ2018 በጀት አመት በእቅድ ለያዛቸው ለተለያዩ ስራዎች የሚውል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከታች በዝርዝር የቀረቡትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የእቃ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሰነድ ቁጥር፡- ቢሞቬ ኢ ኢ ብግጨሰ 01/2018
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህከልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በ2018 በጀት አመት በእቅድ ለያዛቸው ለተለያዩ ስራዎች የሚውል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከታች በዝርዝር የቀረቡትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የእቃ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
1. ሎት አንድ የጽሕፈት (Stationary) እቃዎች
2. ሎት ሁለት የፅዳት እቃዎች
3. ሎት ሶስት የአደጋ መከላከያ (Seafty Materials)
4. ሎት አራት የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መለዋወጫ እቃዎች
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-
1) በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የሆኑ በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
2) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የመንግስት የስራ ቀናት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቢሾፍቱ ሞተር ቬሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በፋይናንስ በኩል የእቃውን ዝርዝር ሁኔታና የጨረታ ሰነዱን በብር 700 (ሰባት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድ በጨረታ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን እና የምትወዳደሩበትን የእቃ አይነት ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል 01 (አንድ) እና ኮፒ 01 (አንድ) ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
3) ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት፡፡
4) ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ የተመሰከረለት 2% የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
5) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልጽ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ማስፈር አለባቸው። ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
6) አሸናፈ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Perfomance Bond) ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል።
7) ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
8) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
9) በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል፡፡
10) ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ለተከታታይ 10 (አስር) የመንግስት የስራ ቀናት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፤
11) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0994521556 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፤
12) ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ ቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ሲንዱስትሪ
ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት
ስልክ ቁጥር፡- 0994521556
ቢሾፍቱ
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ
