የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ ሎት-1 የልብስ ሳሙና፣ ሎት-2 የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና ሎት-3 የጤና ኤክስቴሽን ፎልደር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ለሚ ኩ/ከ/ከ/ ጨፌ ጤ/ጣቢያ 2018 ዓ.ም
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ
የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት፡-
በሎት-1 የልብስ ሳሙና፣ ሎት-2 የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና ሎት-3 የጤና ኤክስቴሽን ፎልደር ሲሆኑ በላይ የተገለጸውን ሥራ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢ/ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ /በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በስተመጨረሻ ተመላሽ የሚሆን ከዚህ በላይ ለተገለጹት ሎቶች /ለሚወዳደሩበት ሎት በመለየት/ በሎት-1 3,000 /ሦስት ሺህ ብር/፣ ሎት-2 3,000 /ሦስት ሺህ ብር/ እና ሎት-3 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ በማስያዝ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በመለየት ፖስታው ላይ በመግለጽ ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ የገዙትን ዋናውን የጨረታ ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ማኅበራት ካደራጃቸው አካል ለሚያመርቱበት ሥራዎች በዋና ሥራ አስፈጻሚ ተፈርሞ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስረከቢያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 5:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ቢሮ ይከፈታል፡፡
6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑትን ላሸነፋበት የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ቼክ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. የተሰረዘ፣ የተደለዘና ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሠነድ ይሰረዛል፡፡
8. ጤና ጣቢያው መ/ቤቱ/ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ስትሞሉ ከነቫት ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ።
አድራሻ፡- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ ከውሀ ታንከር ትንሽ አለፍ ብሎ ባለው ማዞሪያ ላይ በመውረድ ወደ ውስጥ አስፓልቱን 200 ሜ ገባ ብሎ የመጨረሻው አርባ ስልሳ ፊት ለፊት እንገኛለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- /0902 34 04 53 / 0917 70 58 11/ 0904 95 58 01 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ
