የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎችን ግዢ ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎችን ግዢ ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች።
2. በዘርፋ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ኮፒውን እያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
4. የግብር ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ።
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
6. ተጫራቾቾ ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓት 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፈደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 /አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚው ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ፡- 0966886973 / 0917503586 /0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት
