የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ካምፓስ ኮሌጅ በተገነባው የመምህራን ፤ሰራተኞች እና ተማሪዎች ካፌ ህንፃ ግራውንድ ስር የሚገኙ ሱቆችን ለሸቀጣ ሸቀጥ፤ለወንድና ሴት ፀጉር ቤት አገልግሎት በብሄራዊ ግልዕ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ካምፓስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዩ/ጤ/ካ/01/2018
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ካምፓስ ኮሌጅ በተገነባው የመምህራን ፤ሰራተኞች እና ተማሪዎች ካፌ ህንፃ ግራውንድ ስር የሚገኙ ሱቆችን ለሸቀጣ ሸቀጥ፤ለወንድና ሴት ፀጉር ቤት አገልግሎት በብሄራዊ ግልዕ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፧
ሎት.1 የሱቅ ቁጥር 01 የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ፡
ሎት 2 የሱቅ ቁጥር 06 የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ፤
ሉት 3. የሱቅ ቁጥር 04 የወንዶች ፀጉር ቤት፤
ሎት 4. የሱቅ ቁጥር 03 የሴቶች ፀጉር ቤት ኪራይ፧
ስለሆነም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ማለትም፤
1. በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የግብር ከፋይነት የምስከር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለትም ለእያንዳንዱ ሎት 50.000.00 (ሃምሳ ሽህ ብር) በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል!
3. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ህንፃ ቁጥር 05 ቢሮ ቁጥር 12 ከሚገኘው ቢሮአችን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00/ ብር ሶስት መቶ/ በደ/ማ/ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ አካውንት ቁጥር 1000017980517 በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታውን ፋይናንሽያል ዶክመንት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሽገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 10 ቀን በኋላ በ11ኛ ቀን ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበት ሰነድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ጠዋቱ 3፡59 ድረስ ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሱቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል፡፡
6. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ ይኖርበታል።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0913730626 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
◆ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
