Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-11 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ኢኢጽ/ግንአዳ/013/2018

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

የአግልግሎቱ አይነት

 

ብዛት

 

1

 

የወንዶች ሙሉ ልብስ ስፌት

 

1,600

 

2

 

የሴቶች ሙሉ ልብስ ስፌት

 

340

 

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1-    በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (website) ዓትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2-    ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3-    ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4-    ተጫራቾች ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ብር ብቻ) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ሰባ አምስት ቀን የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5-    ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ከቀኑ 9፡00 ላይ ይከፈታል።

6-    መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7-    ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-551-2400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-550-4931 መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Save Tender