የሐምሌ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ለት/ት ሥራ የሚውል የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ በሀገር ውስጥ የተሰራ የስፖርት መምህር ጫማ እና ቱታ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የአላቂ የትምህርት እቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ሐምሌ ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
የግዥ ማስታወቂያ
የሐምሌ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ለት/ት ሥራ የሚውል የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ በሀገር ውስጥ የተሰራ የስፖርት መምህር ጫማ እና ቱታ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የአላቂ የትምህርት እቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች፡-
• በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
• በተጠቀሰው የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
• የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
• ተጫራቾች በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪ በCPO በትምህርት ቤቱ ስም በተጠቀሰው ሎት ለደንብ ልብስ፡- 5,000፤ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች:- 6,000፤ ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች:- 4,000፤ ለአላቂ የፅዳት ዕቃዎች:- 5,000 የጨረታ ማስከበሪ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
• የአሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ በተገለፀበት ከሰባት ቀን ጀምሮ ውል መፈፀምና 10% /አስር ፐርሰንት/ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል።
• ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
• ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
• ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ እና ሌሎች መረጃዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
• ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል። ከስራ ቀን ዉጭ ከሆነ ግን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
• መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ማተሚያ ጀርባ በሞሮኮ ባዝ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር:- 0115-57-44-63//011-5-57-26-81
የሐምሌ ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
