በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ክልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
የኮ/ቀ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መድኃኒዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የ2018 በጀት ዓመት የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የሁለተኛ ዙር የግልፅ የጨረታ መመሪያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ክልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 2. የፅዳት እቃዎች በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
3. ተጫራቾች ይህን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት በየሎቱ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ የድርጅታቹን ማህተም ያረፈበት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
6. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየጋበዝን እንዲሁም አምራች መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉና ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ በጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ የተፈረመ ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በጨረታ ማስረከቢያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን ሎት1፡-14,000፣ ሎት2፡- 26,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማቅረብ አለባቹ።
8. በጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ሲፒኦ በመውሰድ እና ተጫራቶች ውል እንዲዋዋሉ ከመ/ቤቱ ሲገለፅላቸው ያሸነፉበትን የዋጋ ድምር 10% በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
10. ጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ በጥራት የሚበልጥና የሚስተካከል ዋጋ ያለው ዕቃ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል።
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው በጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫ 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል።
12. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡባቸው የተመረጡትን ዕቃዎች ናሙና እስከ ግልፅ ጨረታ ማለቂያ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው።
13. ተጫራቾች ከት/ቤቱ የወሰዳችሁትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በእናንተ የሚሞሉ ክፍሎችን በመሙላት ተመላሽ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እናሳውቃለን።
14. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
15. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኙ ጨረታውን ከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በጦር ኃይሎች በሆላንድ ኤንባሲ ወደ ቀራንዮ አደባባይ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል ፍላንስ ጋር
ስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-69-84
የኮ/ቀ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መድኃኒዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
