የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም አማራ ሪጅን በሎት- 1 ብዛት 8 ስካነር ፣ በሎት- 2 ብዛት 4,096 የልብስ ሳሙና እና 3,294 ሶፍት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አማራ ሪጅን የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ‐አ/አ/ኤ/አ/ፕ/አ/ሪ/ግጨ/001/2018
የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም አማራ ሪጅን በሎት- 1 ብዛት 8 ስካነር ፣ በሎት- 2 ብዛት 4,096 የልብስ ሳሙና እና 3,294 ሶፍት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ባሕር ዳር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 605 በመክፈል ከ10/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/06/2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም አማራ ሪጅን ስም በ15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ላይ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ሙሉ ስም፣ የተጫራቾች ስም ከነአያት፣ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4/6/2018 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 058-220-7620/21 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- ቀበሌ 05 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ባሕር ዳር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አማራ ሪጅን የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም
