አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አላቂ ዕቃዎችንና ደንብ ልብሶችን በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን ከሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ቁጥር 002/793/2018
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አላቂ ዕቃዎችንና ደንብ ልብሶችን በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን ከሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3 የደንብ ልብሶች
ሎት 4 አትክልት ዘር
ሎት 5 ድንኳን አገልግሎት ኪራይ
ሎት 6- የቡና ሴረሞኒ
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይፈልጋል።
1. ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-6 ለተጠቀሱት እቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ እንዲሁም የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ወረቀት ኮፒ በገቢዎች የጨረታ መሳተፊያ ጊዜ የሚገልፅ ደብዳቤ ያለው፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም 50,0000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ ዕቃ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት አስኮ ኖክ ማደያ አለፍ ብሎ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ በመገኘት እያንዳንዱ ሰነድ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 0.5-2 % ካለው ውስጥ (1%)ቱን ያለውን የእቃውን ወደ ብር ተቀይሮ እያንዳንዱ ለሎት1 1% 5000 ለሎት2 1% 10000 ለሎት3 1% 10000 ለሎት4 1% 5000 ሎት 5 1% 5000 ሎት.6 1% 5000 በባንክ በተረጋገጠ (Cpo) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ በማድረግ ጨረታው በአየር እስከ ዋለበት የመጨረሻ ቀን ድረስ እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ በ4/አራት/በፖስታ በማሸግና በግልፅ በመፃፍ ኦርጂናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻልፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የእያንዳንዱ እቃ የሚሸጡበት ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን ፣ስማቸውንና የጨረታ አይነት በመጥቀስ፣ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የተጠቀሱት እቃዎች ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።
7. የጨረታው ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
9. ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቾች ሳምፕል ስታመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል በማይበጣጠስ ወይም በመዳበሪያ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች ለክፍያ ስትመጡ ደረሰኛችሁ ብርሃንና ሰላም የታተመ መሆን እንዳለበት አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ኖክ ማድያ አለፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0984659144
ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ሰነድ በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ ተሞልቶ ማቅረብ አለበት። እንዲሁም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት የጨረታ ሰነዱንና ሳንፕሎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በሚያመርቱት ምርት እና ካደራጃቸው አካል በሚቀርበው ህጋዊ ድጋፍ በንግድ ዘርፉ በተሰማሩበት (በሚቀርበው ድጋፍ ደብዳቤ መሠረት) ይስተናገዳሉ።
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
