አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ ካፖርት፣ ቱታ፣ ሴፍቲ ጫማ ወዘተ...) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- AIC 0011/2018
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ ካፖርት፣ ቱታ፣ ሴፍቲ ጫማ ወዘተ...) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት የደንብ ልብሱን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኩባንያው ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ገዝተው ለሚወዳደሩበት የደንብ ልብስ አይነት እና ብዛት የሚገልፅ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በስራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ- 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከሠዓት 9:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል።
7. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የቅድሚያ ክፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከፈለገ ከታወቀ ባንክ (Unconditional Guaranty) ማቅረብ አለበት።
8. ተጫራቾች ዋጋ ሊያስገቡ ሲመጡ የሚያቀርቡትን የደንብ ልብስ ሳምፕል የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. አንዱ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚታገድ መሆኑን እንገልፃለን።
10. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የደንብ ልብሱን ከ2 ወር ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል።
11. ኩባንያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485 / 0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ
