Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

•        ሎት 1. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ

•        ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ግብአቶች

•        ሎት 3. የተለያዩ ህትመቶች

•        ሎት 4. የኤሌክትሪክ እቃዎች

•        ሎት 5. የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች

•        ሎት 6. የደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ ጫማና የተዘጋጅ ልብሶች

•        ሎት 7. የህንጻ መሳሪያ እቃዎች

•        ሎት 8. የፈርኒቸር እቃዎች

•        ሎት 9. የመኪና ጎማ

በዚህም መሰረት፡-

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ

4.     ውድድሩ የሚሰላው በጥቅል ዋጋ ስለሆነ ለተዘረዘሩት እቃዎች ለሁሉም ዋጋ መስጠት አለበት፡፡

5.     የጨረታ ሰነዱን በብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሒደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

6.     የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO/በመሂ1 ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።

7.     ከብር 10,000 /አስር ሺ/ በላይ ለአገልግሎት ግዥ እና ከብር 20,000 /ሀያ ሺ/ በላይ ለሚገዙ እቃ ግዥዎች 3% የመቁረጥ እና በሥማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።

8.     ለሁሉም ሎቶች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ሥማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።

9.     አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክመንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል።

12. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ሠዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በሆስፒታሉ በመስብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቻው የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡

13. ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋው መሙሊያ ላይ ማግኘት ይቻላል።

14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 09 20 20 56 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡

አድራሻ፡ - በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምእራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡

 

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቁ.2

Save Tender