በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ብርሃን ከተማ አስ/ር የምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት አመት የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን የግንባታ ማቴሪያሎችን፤ የማሽንና ተሽከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍ እና በማወዳደር የተሻለ/ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበው ተጫራች ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ብርሃን ከተማ አስ/ር የምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት አመት የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን የግንባታ ማቴሪያሎችን፤ የማሽንና ተሽከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍ እና በማወዳደር የተሻለ/ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበው ተጫራች ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ እና የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆነ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤ ሁሉም ተጫራቾች በዘርፉ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤
3. ተጫራቾች በሁሉም ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ከፈለጉ የጨረታ ሰነዶችን በየሎቱ ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. የኮንስትራክሽን የግንባታ ማቴሪያሎችን ለሚያቀርቡ ተጫራቾች የብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /C.PO/ በምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
5. የተሽከርካሪ እና ማሽነሪ ጎማዎችን ለሚያቀርቡ ተጫራቾች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ በምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች መሞላት የሚገባውን መረጃ በሙሉ በጥራት በመሙላት፣ በመፈረም እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በደ/ብርሃን ከተማ አስ/ር መዘጋጃ ቤት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ በመምጣት በየሎቱ ብር /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
8. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፤ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤
9. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ በምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፤
10. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 37 74 10/0920 85 48 81 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የምንሊክ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
