Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ቦረና ጉጂ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-3350901
  • Websitehttps://www.oromiaforest.et/
  • Deadline19 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-19 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Materials , Stationery Materials

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ 2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ 2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1.     የጽህፈት መሳሪያዎችን

2.     የልማት ዕቃዎች

3.     የፅዳት ዕቃዎች

በዚሁ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

1.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

3.     የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ ቁጥር የተሰጣቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ 2% በተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     የጨረታው ሳጥን በ11 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ሞዴል ወይም አይነት በጨረታው ሰነድ ላይ በግልጽ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት የሁሉንም ናሙና ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ማንኛውም ተጫራች ለመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት፡፡

8.     በተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ያሳግዳል፡፡

9.     ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ከላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊ መረጃዎች አሟልተው ባልተገኙ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡

10. አሸናፈው ያሸነፈውን እቃ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 046-3350901 (09894774) ደውሎ መጠይቅ ይችላሉ፡፡

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender