Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውል የታሸገ ውሃ እና የምግብ ቤት መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎችን ለዋና መ/ቤት እና ለደብረዘይት የስልጠና ማዕከል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 010/18

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውል የታሸገ ውሃ እና የምግብ ቤት መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎችን ለዋና መ/ቤት እና ለደብረዘይት የስልጠና ማዕከል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚወዳደሩ

የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (ሁለት መቶ ብር) አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመከፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታው ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ብር በሲፒአ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ህጋዊ ሰነዶች ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ይህ የጨረታ ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡-

አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598/0118-69-4931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

 

Save Tender