ት/ቤታችን ስኩል ኦፍ ሪደምሸን አ.ማ በ2018 በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
School of Redemption (ስኩል ኦፍ ሪዴምሽን አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ት/ቤታችን ስኩል ኦፍ ሪደምሸን አ.ማ በ2018 በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን እቃዎች ማለትም፡ -
- ለቢሮና ለተማሪዎች ማስተማሪያ የሚሆኑ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ግዥ
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- የፔዳጎጂ መስሪያ እቃዎች
- የት/ቤት ግቢ የቴራዝ ንጣፍ ስራ ከነሙሉ ግብዓቱ
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በተ.ቁ. 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000፣ በተ.ቁ. 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000፣ በተ.ቁ. 3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000፣ በተ.ቁ. 4 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 እና በተ.ቁ. 5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000፣ በእያንዳንዱ ተ.ቁጥር በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ለየብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባችኋል:: በዚህም መሠረት በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 1,000 ብር በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ:: ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ8ኛው ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
ሆኖም ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻው ቀን ባለመገኘታቸው ጨረታውን አያስተጓጉለውም። አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታው የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- 0906 96 94 96 ይደውሉ::
ስኩል ኦፍ ሪዴምሽን አ.ማ
