Tender Detail

Tender Details


በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በከተማ አስተዳደሩ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በከተማ አስተዳደሩ በጀት

  1. ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች
  2. ሎት 02 የጽዳት እቃዎች
  3. ሎት 03 የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማ ከነከመነዳሪያቸው
  4. ሎት 04 ሲሚንቶ፣ የተለያዩ ብረቶችና እና ሌሎች ማቴሪያሎች

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት በጥቅል ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በከፊል ወይም ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡
  6. እያንዳንዱ እቃ በስፔስፊኬሽኑ መሠረት መሞላት አለበት፤
  7. የሚገዙትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፣
  8. በጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ጋራንት/ በስማቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በሚል አድራሻ በስማቸው ከኦርጅናል ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስያዝ አለባቸው።
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትርበስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ፡ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፣
  13. አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአሉት 5 የስራ ቀን በኋላ በአሉት 5 ተከታታይ ቀን ውስጥ መዋዋልና በውሉ መሰረት እቃውን የማጓጓዣ ወጭን ችሎ በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት ፡፡
  14. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲ.ፒ.አ. ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የሚያስይዙት ዋስትና ጊዜ እቃው ተጠናቆ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፣
  17. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  18. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን

 

Save Tender