Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስፖርት መምህራን ትጥቆች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፃሕፍት፣ ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስፖርት መምህራን ትጥቆች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፃሕፍት፣ ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና ስራዎችን ማስራት ይፈልጋል፡፡

ጨረታው ከመከፍቱ በፊት በቀረበው የተጫራቾች ለሚወዳዳሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡ የገዙትን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው በመፃፍ ለየብቻ በማዘጋጀት ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ጨረታው

ለእያንዳንዱ ሎት የምታቀርቡት የሲፒኦ መጠን

6211=6,588 (ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር)

6212=6,217 (ስድስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ሰባት ብር)

6213=388 (ሶስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር)

6215=10,354 (አስር ሺህ ሶስት መቶ ሀምሳ አራት ብር)

6218= 2,678 (ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስምንት ብር)

6219=3,224 (ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሀያ አራት ብር)

6313= 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር)

የጨረታ መስፈረት ከዚህ በታች እንደሚመለከተው ይሆናል

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የዘመኑ የታደሰ ግብር ከፋይ መለያ ያላቸው
  • የአቅራቢነትን ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት ቤት የፋይናንሰ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡00 ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡ ጨረታው በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሳጥን ተዘግቶ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የህብረት ችቦ የመ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል።

የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች ከታወቀ በኃላ ለተሸናፊዎቹ ያሲያዙት ገንዘብ ወዲያው ይመለስላቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊዎቹም ተለይተው በተገለፀው በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎቹ ደግሞ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊዎች በገቡት ውል መሰረት ዕቃዎችን ተቋሙ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አላባቸው፡፡ መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራቶች አምራች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ ማምጣት አለበቸው። በድጋፈ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑ እናሳውቃለን።

አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ሳሪስ አቦ አዋሽ ቆዳ አጠገብ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 011 443 1698

 

በአቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender