በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት በዞን አስተዳደር ስር ለሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የሚሆን ጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በንጥል ዋጋ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት በዞን አስተዳደር ስር ለሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የሚሆን ጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በንጥል ዋጋ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው
- የአቀራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣
- የሚጠየቁ ናሙና አይነቶችን ማቅረብ የሚችል፣ ናሙናዎችን ዞን ፋይናንስ ማየት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የተጠየቁ ናሙናዎችን በጨረታ ሰዓት ይዘው መቅረብ አለባቸው
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ከጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገኛሉ።
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ እስከ ሳውላ ከተማ ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ንብረት ክፍል አምጥቶ በተያዘው ናሙና መሠረት ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3:00 ታሽጎ በዕለቱ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
- በተጨማሪ ማብራሪያ - የስ.ቁ 09-13-32-97-28 ይደውሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ
