Tender Detail

Tender Details


በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ

  • የፅዳት እና የእስቴሽነሪ እቃዎች Lot. 2
  • ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (Office Furniture ) Lot 3
  • የሠራተኞች ደንብ ልብስ (Uniform and protections) Lot 4 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች በድርጅቱ ጽ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን ፤ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በስማቸው ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ። የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ 1,000.00 ብር (አንድ ሺህ) በመክፈል ከድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመምጣት ለጨረታ የተዘጋጀ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም በፌዴራል ገ/ኢ/ትብብር ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ኢ ትብብር ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ ውል ማስከበሪያ (ዋስትና (10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በኦርጂናል እና በኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን ሲሆን ቀጥሎ የሚውለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት አድራሻ በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 02 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ - 0911798879/

0912895258/0969348673

 

በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ

ቡራዩ

 

Save Tender