Tender Detail

Tender Details


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በዩኒሴፍ የገንዘብ ድጋፍ ለት/ቤቶች ለMHH አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ስቴሽነሪና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በዩኒሴፍ የገንዘብ ድጋፍ ለት/ቤቶች ለMHH አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ስቴሽነሪና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ፍቃድ ኖሯቸው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin number/ ቫት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ /ሲፒኦ/ 10,000 ብር፣ ለሎት ሁለት 25,000 ብር፣ ለሎት ሶስት ብር 15,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል።
  5. የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቤ/ጉ/ክ/መ ጤና ቢሮ ቁጥር 502 መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  6. መወዳደሪያ ዋጋ መሞላት ያለበት በኢትዮጵያ ብር መሆን አለበት።
  7. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎችን ሙሉ በሙሉ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው ስፔስፊኬሽን /specification/ መሰረት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
  9. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት እቃውን በራሱ ወጪ በቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በመግዛት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውን በ16 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ እለት ከቀኑ 8፡30 ስለሚከፈት በቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ቁጥር 502 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፣
  11. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገም በስልክ ቁጥር 05770750839/ 09-25-79-82-03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ

 

Save Tender