በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆነ ተወዳዳሪዎች ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድፍጤጣ/ግልጽ/ጨ/02/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆነ ተወዳዳሪዎች ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት1. ደንብ ልብስ (ጫማዎች)
- ሎት2. የፅህፈት መሳሪያዎችና የኤሌክትሪክ እቃዎች
- ሎት3. የቢሮ ፅዳት መገልገያ እቃዎች
- ሎት4. የህክምና መሳሪያዎች
- ሎት5. የመኪና ጎማ፣ ቅባቶችና የወንበር ልብስ
- ሎት6. የሰው መድኃኒት እና ሪኤጀንቶች
- ሎት7. የእንጨት ውጤቶች
በዚህም መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን የቴክኒክ መመዘኛ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች አንድትሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በዘርፉ የተሰማሩ የ2018ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመንግስት ግዥ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የታደሰ ግብር ከፋይነት ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ያለው እና ለመድኃኒት ተወዳዳሪዎች የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎት ክፍያ በ2ኛ ብሎክ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 901 በመፈጸም የጨረታ ሰነድ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 907 መውሰድ አለባቸው።አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለሰነድ ግዥ እና ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚያመርቱት ግብዓት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ለ10 (አስር ቀን) የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በጤና ጣቢያው 2ኛ ብሎክ 3ኛ ፎቅ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ አዳራሽ ቁጥር 803 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም የጨረታውን መክፈቻ የሚያስተጓጉል አይሆንም።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጋጠ /CPO/ ቢድቦንድ ወይም አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚያመርቱት ግብዓት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሲሆን ለሎት1 ብር 5,000.00፣ ሎት2 ብር 5,000.00፣ ሎት3 ብር 5,000.00 ብር፣ ሎት4 ብር 20,000.00፣ ሎት 5 ብር 10,000.00፣ ሎት 6 25,000.00፣ እና ለሎት 7 ብር 10,000.00 በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም በማሰራት ከሚያቀርቡት ቴክኒካል መረጃ ጋር አያይዘው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስም፣ ማህተም ፊርማ በማድረግ የጨረታውን አይነት ሎት በግልጽ በመግለጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ቴክኒካል መመዘኛ መረጃዎች በኮፒ ፋይናንሺያል ፖስታ ውስጥ ብቻ ተያይዞ መቅረብ አለበት። በተጨማሪም የህክምና ቋሚ እቃዎች የእቃ ስፔሲፊኬሽን ለብቻው በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት። በሁሉም ሎቶች ላይ ዋጋ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም የእቃ specification በራስ መቀየር በዛ እቃ ወይም አገልግሎት ላይ ተወዳዳሪ አያደርግም።
- ተጫራቾች የእቃ ናሙና እና በፎቶ ለተጠየቁባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎት ናሙናውን ቀድመው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ኮድ በማሰጠት በዝርዝር አስመዝግበው ማቅረብ አለባቸው።
- ጤና ጣቢያው በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በጨረታ በግዥ ትዛዝ ላይ 20% የመጨመር እና 20% የመቀነስ መብት አለው። እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉን ከተገለጸለት በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ከጠቅላላ ዋጋ ሲፒአ በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም አሰርቶ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ጤ/ጣቢያው አድራሻ መጋዘን አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
- ጤ/ጣቢያው ለሚፈጽመው ግዥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ጠመረጃ
አድራሻ፡- ገርጂ መብራት ሀይል ሰብስቴሽን ጀርባ ኮብል ስቶን መንገድ ገባ ብሎ
ስልክ፡- 09-88-05-3333
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ
