Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ
  • Address , Phone: 0118346552
  • Website
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-28 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ብ.ፋ.ኢ/ብ.ግ.ጨ/001/2018

 

ግዥ ፈፃሚ አካል ስም፡- በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ

የዕቃ ግዢው ዓይነት፡-

  • ሎት 1 የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎች
  • ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች

የተጫራቾች መመሪያና ግዴታዎች፦

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. ተጫራቾች በወጣው ጨረታ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩና የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣
  4. በግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፤
  5. ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ
  6. ከጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር የሚመጡ እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾችን ጨምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ /VAT/ን ጨምሮ ብር 2% ከታወቀ ባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ብቻ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያያዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል። በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው።
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  9. የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መካኒሳ መካነ ኢየሱስ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮአችን በግዥ ክፍል ቢሮ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት በግዥ ክፍል ቢሮ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-10፡30 የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
  11. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል።
  13. ጨረታው ጠዋት 4፡30 ላይ ተዘግቶ 4፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።
  14. ጨረታውን አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት።
  15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መመሪያ መሰረት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  16. የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ በቢሮ ስልክ ቁጥር 011 834 6552 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ

Save Tender