Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline12 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-12 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Sanitary Ware

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለመንገደኛ ተርሚናል አገልግሎት የሚውል ትልቁን የመፀዳጃ ቤት ወረቀት /Jumbo Commercia Toilet Paper/ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: SSNT-T593

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለመንገደኛ ተርሚናል አገልግሎት የሚውል ትልቁን የመፀዳጃ ቤት ወረቀት /Jumbo Commercia Toilet Paper/ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. የለስላሳ ወረቀቶች እና ተያያዥ ምርቶች የሀገር ውስጥ አምራች የሆኑ፣
  2. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ሁለት (2) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T593 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) "በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ -

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡- +251-115-17-89-18

ኢ-ሜይል:ESAYASTS@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender