በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 01 የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ሎት 1. ደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 4. የፅዳት እቃዎች ሎት 5. ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 6. ጥገና፣ ሎት 7. የጭነት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡ 02/2018
በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 01 የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ሎት 1. ደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 4. የፅዳት እቃዎች ሎት 5. ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 6. ጥገና፣ ሎት 7. የጭነት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የሥራ መስኩ በጀረባ ገፅ ይመልከቱ የሚለውን በትክክል የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡
- የመንግሥት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎችን የምተሟሉ ተጫራቾች በስራ ቀን የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ዋጋ 2% ሲፒኦ በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ/ት/ቤት ስም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር በፋይናንስ ቢሮ ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ /በፍሉድ የጠፋ/ ሰነዱ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ለጨረታ የሚወዳደሩባቸውን ሰነዶች ኦርጅናል ና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ዉጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም።
- በጨረታው ተወዳድረው ከአሸነፉ በኋላ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅድሚያ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
አድራሻ፡- ዋናው ፓስታ ቤት ከፍ ብሎ ትራኮን ህንፃ ፊት ለፊት /ሊሴ/ገ/ማርያም ት/ቤት ጎን ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር፡- +2511-1-26-28-39
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ ቢሮ የአራዳ ክ/ ከተማ ት/ፅ/ቤት በወረዳ 01 ጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
