Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ኮንሶ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-773-01-86
  • Website
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityለጽ/መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/፣ ለፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Stationery Materials , Electronics Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በመንግስት መደበኛ ገንዘብ እና ካፒታል ገንዘብ ምንጭ ከዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሰበሰበው የግዥ ዕቅድ ፍላጎት መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ቁጥር (ኮዞፋመ-ግጨ/ዕአግ/001-13ጨ/-2018)

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በመንግስት መደበኛ ገንዘብ እና ካፒታል ገንዘብ ምንጭ ከዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሰበሰበው የግዥ ዕቅድ ፍላጎት መሠረት:-

  1. ሎት 1//Lot one/ የጽህፈት መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ፣
  2. ሎት 2/ /Lot two/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣
  3. ሎት.3/ /Lot Three/ የፈርንቸር ዕቃዎች ግዥን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በጥቅምት 1/2017 ዓ፡ም ላይ አሻሽለው ያወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 71/2017 አንቀጽ 55 በንዑስ አንቀጽ 1፣2 እና 3 መሠረት በነዚህ ሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ እንዲሁም በመደበኛ ጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠየቁትን መሠረታዊ ነጥቦች ወይም የህግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ህጋዊ ግብር ከፋዮች /አቅራቢዎችን/ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በሙሉ፡

1/ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ ያላቸው

2/ በዘርፉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው

3/ በዘርፉ /TIN Number/የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው

4/ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ወይም እንደ ሁኔታው የቲኦቲ /ተመዝጋቢ የሆኑ)

5/ በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው

6/ ማህበራት ከሆኑ ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው

7/ ማህበራት መደራጀታቸውን የሚገልጽ ካደራጃቸው መ/ቤት ህጋዊ የድጋፍ ዳብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

8/ ተጫራቾች፡- በሶስቱም ሎቶች የጨረታ ዝርዝር ወይም መደበኛ የጨረታ ሠነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በመለጠፍ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ የሠነድ ሽያጭ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ር ዳይረክቶሬት ቢሮ ቁ.11 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

9/ ተጫራቾች በሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ /CPO/ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለጽ/መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/፣ ለፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር በፖስታ አሽገው ለኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ብሎ በአድራሻ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና 1 ኮፒ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ጋር በትክክል በታሸገ በአንድ ኤንቨሎፕ ወይም የእናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ማህተም በማሳረፍ፣ አድራሻ በመግለጽና በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11/ ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 6፡00 ላይ ታሽጎ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች የጨረታ አከፋፈትን በተመለከተ የቴክኒካል ኦርጅናል ፖስታ በመጀመሪያ ደረጃ ይከፈታል በጨረታ ማስታወቂያ መሠረት የተቀመጡ ቴክኒካል የግምገማ ከተገመገመ በኋላ ቀጥሎ የፋይናንሻል ኤንቨሎፕ/ፖስታ/በመመሪያ መሠረት ተከፍቶ ይነበባል የተደረገው ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ጥናት ጋር በማመሳከር ግምገማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

12/ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ የማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

13/ አሸናፈው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሰነድ 10% በማስያዝ ባሸነፉበት የስራ የውል ማስከበሪያና ተመጣጣኝ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ይዘው ቀርበው 15 ስራ ቀናት ውስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

14/ ተጫራቾች ጨረታ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው ይከፈታል በተባለው በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

15/ ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም ፡፡

16/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17/ ተጫራች የጨረታ ሠነድ ዋጋ ማቅረቢያ እንዲሁም ከመደበኛ የጨረታ ሠነድ በተጨማሪ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ገዥ ይሆናል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡- 046-773-01-86/09 06 48 25 47/09 20 98 00 15/09 10 82 59 12/ ደውለው  ይጠይቁ የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ -ካራት

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

 

Save Tender