Tender Detail

Tender Details


በአ/ሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም

 

በአ/ሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን ማለትም፣

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሉት 3. የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4. የህትመት እቃዎች
  • ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የኢፌዲሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተእታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና (TIN No) ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00: 10፡00 ሰዓትና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 4) በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /finatioal/ ሰነድ ፣እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ መፈረም እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።  ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 09 22 45 04 40/09 10 70 49 72 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ በር 3 ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 31 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender