Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0113659360
  • Website
  • Deadline22 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2%
  • opening date2025-12-22 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥርማዕ/ ኢት/ ትራ/መን/ል/ ቢሮ መደ 002/2018

 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ፡፡
  4. የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፡፡
  5. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. በኦንላይን የተመዘገበ፡፡
  7. የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቬሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጂናል/ ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት ያለባቸውም፣ ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ሰነድ፣ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና CV ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በዋናው /አሪጅናል/ ሆኖ ኮፒ ኤንቬሎፕ ውስጥ ከፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
  10. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር የሚውል ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ላይ በተጫራች ፊት ተከፍቶ በንባብ ይሰማል ፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል ፡፡ ማንኛውም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንከ ዋስትና የሚቀርብ: በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ /አቅራቢ/ዎች/ ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0991415433 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ቢሮ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  14. አቅራቢዎች በነጠላ ወይም በጅምላ መርጦ መጫረት ይችላሉ፡፡

 

የቢሮ አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

Save Tender