የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የቢሮ ውስጥ መገልገያ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍቼ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የቢሮ ውስጥ መገልገያ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና እቃዎች ፤ ልዩ ልዩ እቃዎች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚያቀርቡ እንዲሁም የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ) ከባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ የማኅበራዊ ዋስትና ደብዳቤ ከአደራጀው አካል በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማፃፍ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሽጥበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ የማስጫንና የማውረድ ወጪን መቻል ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0111 350 953 በመደወል እንዲሁም የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍቼ
