በአብክመ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-
- የጽህፈት መሳሪያና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የኤክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ፈርኒቸር የቢሮ መገልገያ
በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነ ፡-
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግዥያችን መጠን ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተራ ቁጥር 1/ 50,000 ብር በተራ ቁጥር 2/ 5,000 ብር በተራ ቁጥር 3/ 20,000 ብር በተራ ቁጥር 4/ 10,000 ብር የተጠቀሱት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣባት 23/3/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 08/4/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብ/ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻው በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ከ23/3/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም እስከ 08/4/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡35 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።፡
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ውድድር በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹት በሎት ሊሆን በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተገለጸው በነጠላ ዋጋ መሆኑን እናሳውቃለን።
ከሚሴ አድራሻ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ ላይ እንገኛለን፡፡
ስልክ ቁጥር 0335542119 ወይም 0335540364 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የአብክመ የኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ
