በቂርቆስ ክ/ከተማ የወርሃ የካቲት ቅድመ አንደኛ/መካ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት አልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወርሃ የካቲት ቅድመ አንደኛ አንደኛ/ መካ/ደ/ት/ቤት
2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ የወርሃ የካቲት ቅድመ አንደኛ/መካ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት አልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1. የደንብ ልብስ 6211 …..5000ብር
- ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች የፅህፈት መሳሪያዎች 6212…..4212ብር
- ሎት3. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች 6218…..3250ብር
- ሎት4. የፈጠራ ስራ ዕቃ መግዣ 6223…..500ብር
- ሎት5. ለፕላንት ማሽነሪ እና መሳሪያ መግዣ 6313…..4900 ብር
- ሎት6. ለህንፃ ቁሳቁስና ለተጣጣሚዎች መግዣ 6314…..1750 ብር
- ሎት7. የጭነት አገልግሎት 6255…..1250 ብር
- ሎት8. የደንብ ልብስ ስፌት…..…..…..1000
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ ዕሴት (ታክስ) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ዋጋው ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ያባይሆን ለሚፈጠረው ክፍተት ሃላፊነቱን ነጋዴዉ እንደሚወስድ እናሳዉቃለን
- ጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ከላይ በተዘረዘረው ሎት ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአጠቃላይ 100 ብር የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በወርሃ የካቲት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ቢሮ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲያመጡ ሲፒኦውን CPO) እና ተያያዥ መረጃዎችን ደግሞ የጨረታውን ሰነድ ኮፒ ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት እና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም የሚያቀርቡትን እቃ ዋጋ ከነቫቱ መሙላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው ቀን 11፡00 ተዘግቶ ከ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የ11ኛው ቀን ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻችን
- ቄራ በርታ ኮንስትራክሽን ከፍ ብሎ ወደ ቂርቆስ መሄጃ መንገድ ላይ፡፡
- በላንቻ በኮንኮርድ ገባ ብሎ ወረዳ 4 ጽ/ቤት አለፍ ብሎ በስተግራ ባለው አስፓልት መንገድ ወደ ቄራ መውጫ ላይ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር : 011-4-16-35-63/ 011-4-70-37-95/ 011-4-70-37-89
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወርሃ የካቲት ቅድመ አንደኛ/መካ/ደ/ት/ቤት
