Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደቡብ ቅ/ጽ/ቤት/002/2018

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል

 

ሎት

የእቃው የአገልግሎቱ አይነት

ምብራሪያ

ሎት 1

አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተር ቀለም

 

ሎት 2

የሰራተኞች የደንብ ልብስ

 

ሎት 3

የጽዳት ዕቃዎች

 

ሎት 4

የተሽከርካሪ ጌጣጌጥና የመኪና ጎማ

 

ሎት 5

የቢሮ ማስዋቢያ (መጋረጃ)

 

 

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህም መሰረት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማሟላት እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሎት 1. 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2. 6,000 (ስድስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 3. 2,000 (ሁለት ሺህ)፣ ለሎት 4. 6,000 (ስድስት ሺህ) እና ለሎት 5. 6,000 (ስድስት ሺህ) በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሲሆን ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ ከክፍያና ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በግልጽ መለየት አለባቸው። በግልፅ ካልተለየ የቀረበው ዋጋ ከቫት ጋር ነው ተበሎ ይወሰዳል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ከጥዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
  4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡40 ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ/ከተዘጋ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
  7. ተጫራቾች የሚጫራቱበትን አገልግሎት የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ በሚያስኬደው መንገድ ሀዩንዳይ ፊት ለፊት በሚገኘው ሃና ፉሪ ግንባታ ሳይት ውስጥ

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-66-42-82-98/09-12-00-72-07/ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender