በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም፡- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃ፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃ፤ ሎት 4 የኤሌክትሪክ ዕቃ፤ ሎት 5 የተለያዩ የህትመት ስራ፤ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፤ ሎት 7 የቧንቧ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም፡- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃ፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃ፤ ሎት 4 የኤሌክትሪክ ዕቃ፤ ሎት 5 የተለያዩ የህትመት ስራ፤ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፤ ሎት 7 የቧንቧ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው በየሎቱ ማስገባት እና ማቅረብ አለባቸው።
- ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽ/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም አርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናንስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታ ማስገባት ትችላላችሁ። ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያው ይታሸጋል ወዲያው 4፡10 ላይ ይከፈታል።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር8 በሞባይል 0913675704 /0913034113 /0913023571 ቁጥር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ 05 / አምስት / ቀን ይቆያል።
- የመክፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው።
- ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ ከግቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው።
- ውድድሩ የምናወዳድረው በጥቅል ነው።
ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
