Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ቤንች ወረዳ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0966886973
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው አጠቃላይ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎችን ግዢ ለመፈፀም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው አጠቃላይ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎችን ግዢ ለመፈፀም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል /ምትችል
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል
  5. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አሥር የሥራ ቀናት/ ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰአት ላይ ታሽጐ በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፍታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፈደል መግለጽ አለባቸው፡፡ በፊደል እና በአሀዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሦስት መቶ /300/ በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 /አሥር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ /1/ ኦርጂናል እና ሁለት /2/ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ /1/ ኦርጅናል እና ሁለት/2/ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግልጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
  11. ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን ከደ/ቤ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር 0966886973 / 0917503586 0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender