የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 01 እስቴሽነሪ፣ ሎት 02 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 03 የጽዳት ዕቃዎችና፣ ሎት 04 የሞተር ሳይክል
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በገቢዎች ሚኒስቴር የምዝገባ ሠርተፍኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 209 በመምጣት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሎት 01 /ስቴሽነሪ/ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፣ ሎት 02 /ለኤሌክትሮኒክስ/ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ፣ ሎት 03 /የጽዳት ዕታዎች /5,000/ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 04 /የሞተር ሣይክል/ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱንም በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና በመለየት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 እስከ 6:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። በ6፡31 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፕላንና ልማት ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ውስጥ ቢሮ ቁጥር 209 ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀላት ቀን ጀምሮ በ03 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ 5% ቼክ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ከፕላንና ልማት ቢሮ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይፈርም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ
