Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security8000 /ስምንት ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-01 00:00:00
  • Categories Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በተያዘለት በጀት የመኪና መለዋወጫ እና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በተያዘለት በጀት የመኪና መለዋወጫ እና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ከ05/03/2018 እስከ 19/03/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለሰነዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 8000 /ስምንት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ከሆነ ኦርጅናሉን፣ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡
  8. የመኪና መለዋወጫ እና ጎማ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 22/03/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መከፈቻው ጊዜ የበዓል ቀን፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  10. በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በስልክ ቁጥር 0333 519107 ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  13. የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው፡፡
  14. መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

 

Save Tender