ቅ/ጽ/ቤታችን በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ውስጥ አራብሳ ሣይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ ሲሆን፣ ለቅ/ፅ/ቤቱ የተለያዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡ ሰ/ቅ/ጽ/ቤት001/2018
ቅ/ጽ/ቤታችን በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ውስጥ አራብሳ ሣይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ ሲሆን፣ ለቅ/ፅ/ቤቱ የተለያዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ሎት 1 አላቂ እና ቋሚ የቢሮ መገልገያ እና የፅህፈት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 2 የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 3 የጽዳት አቃዎች ግዥ
- ሎት 4 የተሽከርካሪ ቅባቶች፣ ጌጣጌጦች፤ መለዋወጫዎች እና የመኪና ጎማ ግዥ
- ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የቢሮ ውበት መጠበቂያ እና የአይ ሲ ቲ እቃዎች ግዥ
- ሎት 6 የህትመት አገልግሎት ግዥ
በዚሁ መሰረት በዘርፉ የተሰማራችሁ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ /ክሪላንስ/፣ የፌዴራል ግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ምዝገባ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የማይመለስ ኮፒ
- የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ ቀርባችሁ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከቅ/ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ የቴክኒክ ሰነድ ኮፒ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ /የፋይናሽያል/ ፖስታ ኦርጅናል አጠቃላይ በ2 ፖስታ በማሸግ እና በመለየት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ ደረሰኝ/ በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለዕቃ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን እቃ 2% ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ለአገልግሎት ማለትም ለሎት 6 ተጫራቾች 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ ያቀርባል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ፕ/ጽ/ቤቱ ድረስ ናሙና /ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የመኪና ጎማ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሳምፕል በሚታይ ፎቶ የሚቀርብ ሲሆን ሳምፕል አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ባለበት ቦታ ድረስ በመሄድ በመስሪያ ቤታችን ባለሙያ የሚታይ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ናሙና ባልታየባቸው እቃዎች መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በግርጌው ስም፣ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ዝርዝር የጨረታው መስፈርቶችን በጨረታ ሠነዱ ላይ በመመልከት አስፈላጊ መረጃዎችና ማስረጃዎችን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ዓመት በዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ እንዲሁም አስቸኳይ ስብሰባ ካጋጠመ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ።
- በዚህ የጨረታ መመሪያ ያልተካተቱ ሌሎች ሁኔታዎች በሀገሪቱ ሕግና ደንብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 ዓ.ም መሰረት የሚታይ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- በመ/ቤታችን ቅዳሜ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እንደ አንድ የሥራ ቀን ይቆጠራል፡፡
አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰሜን ቅ/ጽ/ቤት አራብሳ ሳይት ሰፈራ አደባባይ ከፍ ብሎ።
ስልክ 0919418181
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
