የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመጻሕፍት በ2018 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ሥራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የነዳጅ ቦቲ መኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Abrehot Library (አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመጻሕፍት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመጻሕፍት በ2018 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ሥራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የነዳጅ ቦቲ መኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሱትን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ ሎት 1 የመኪና ኪራይ 50,000፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት 20,000.00፣ ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ እቃዎች 50,000.00፣ ሎት 4 የነዳጅ ቦቲ መኪና ኪራይ 10,000 ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከቢሮአችን ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር ቢ35 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና ቢሮ ቁጥር ቢ 21 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦርጅናል ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር s9 ይከፈታል፡፡ ሆኖም እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በተገለፀ ከ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት፣
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0923026736
አድራሻ 4 ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመጻሕፍት
