በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለመምሪያዎች እና ለጽ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ለ1ኛ ዙር በሎት ጠቅላላ ድምር ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት2 ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት3. የጽዳት እቃ፣ ሎት4. የመኪና ጎማ፣ ሎት5. ሞተር ብስክሌት ጥገና፣ ሎት6. የመኪና ዲኮር፣ ሎት7. የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት8. የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት9. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት10. የኮምፒዩተር ተዛማጅ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለመምሪያዎች እና ለጽ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ለ1ኛ ዙር በሎት ጠቅላላ ድምር ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት2 ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት3. የጽዳት እቃ፣ ሎት4. የመኪና ጎማ፣ ሎት5. ሞተር ብስክሌት ጥገና፣ ሎት6. የመኪና ዲኮር፣ ሎት7. የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት8. የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት9. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት10. የኮምፒዩተር ተዛማጅ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለውና ማቅረብ የሚችል
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህትም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሳምፕል ላልቀረበባቸው የግዥ ሎት በተጠየቀው ዝርዝር መሰረት ያሸነፈው ድርጅት ላምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሆኖም ያቀረቡት ሳምፕል ውል ይዘው ዕቃው ገቢ ከተደረገላቸው በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ድሮው ንግድ ባንክ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የኮምፒተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና በደ/ማ/ከ/አስ/መምሪያዎች ቢሮ ድረስ በመምጣት መጠገን የሚችል እና የሞተር ብስክሌት ጥገና ደብረማርቆስ ከተማ ጋራዥ ያለው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ስም በተዘጋጀ መሂ-1 ደረሰኝ 1% በመቁረጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት የቀድሞው ዋናው ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ በአየር ላይ ይውላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው በተገኙበት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሠዓት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ን/ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ይዞ በመምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587713362
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
