Tender Detail

Tender Details


የኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከ/አስ/ የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን በቢራሮ ክፍለ ከተማ ስር ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 01 - ቋሚ እቃ/ፈርኒቸር፣ ሎት 02 - የፅህፈት መሳሪያ ሎት 03 - የፅዳት እቃ፣ ሎት 04 - የደንብ ልብስ አልባሳት፣ ሎት 05 - የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 06 - የኤሌክትሮኒክስ እቃ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት


 

የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ/ቁጥር፡-ቢ/ክ/ከ/አስ/ግ/ፋ/153/2018/

 

የኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከ/አስ/ የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን በቢራሮ ክፍለ ከተማ ስር ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 01 - ቋሚ እቃ/ፈርኒቸር፣ ሎት 02 - የፅህፈት መሳሪያ ሎት 03 - የፅዳት እቃ፣ ሎት 04 - የደንብ ልብስ አልባሳት፣ ሎት 05 - የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 06 - የኤሌክትሮኒክስ እቃ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እሰከ 2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅርብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ከሎት 01 እስከ ሎት 06 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር እፍ ክሬዲት ዋጋ 1% ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት በመክፈል ከቀን 28/02/2018 ዓ.ም እስከ 12/03/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከቀን 28/02/2018 ዓ.ም እስከ 12/03/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በቀን 15/03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታው መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነም የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም። ያልተሞላ ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪ መ/ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ5/አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 14 06 55 89 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
  12. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመ/ቤቱ ግዥ የማይሳተፉ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  13. ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘ ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% /ሀያ በመቶ/ መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል ይሆናል፡፡
  14. ለሎት 04 እና ለሎት 05 በክ/ከተማው ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በተቀመጠው ሳምፕል /ናሙና/ መሰረት በማየት ሰነዱን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በኮምቦልቻ ቢራሮ ክ/ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ክ/ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

 

 

Save Tender