በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባ/ል/ቅ/ጽ/ቤትአስፍዳ2018/001
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1. የደንብ ልብስ
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 4. የፕሪንተር ቀለሞች
- ሎት 5. የመኪና ጎማ እና የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች
- ሎት 6. የአይሲቲና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 7 የፈርኒቸር ዕቃዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፋ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት
የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ።
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ ከአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት፣
- ለሎት 1፣ 2 ፣ 3 እና 4 በእያንዳንዳቸው በተናጥል የ5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር) CPO ለሎት 5፣ 6 እና 7 ለእያንዳንዳቸው በተናጠል የ10,000 ብር (አስር ሺህ ብር) CPO
- ባለሥልጣን መሥሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ዳሽን ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 06
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-557-51-05-05 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
