Tender Detail

Tender Details


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2017 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 5 የማሽነሪ እቃዎች፣ ሎት 6 የህትመት የግብዓት እቃዎች፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ፣ ሎት 8 የስንዴ ዱቄት ግዥ እና ሎት 9 የምግብ ምርት እህሎች በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ


 

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የግዥ መለያ ቁጥር E/M/T/C/E NCB/01/2018

 

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2017 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 5 የማሽነሪ እቃዎች፣ ሎት 6 የህትመት የግብዓት እቃዎች፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ፣ ሎት 8 የስንዴ ዱቄት ግዥ እና ሎት 9 የምግብ ምርት እህሎች በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

  1. በዘረፉ የወጣና ለዘመኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ኮፒ፤ በማንኛውም የመንግሥት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
  2. ማንኛውም፣ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም።
  3. ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ሁሉም (ሶስቱም) ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት 4፡01 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ቢያንስ 90 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት።
  8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታከስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት። የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግሥት ታክስና ወጪን አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
  9. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0908085555 ወይም 0918053797 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ

 

Save Tender