በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ደንብ ልብስ፣ የፅዳት እቃ፣ የመብራት እቃ እና የፅህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ደንብ ልብስ፤ የፅዳት እቃ፣ የመብራት እቃ እና የፅህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ/ች
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ነች፣ ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው
- ሎት 1. ደንብ ልብስ
- ሎት 2. የፅዳት እቃ
- ሎት 3. የመብራት እቃ
- ሎት 4. የፅህፈት መሳሪያ
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሆስፒታሉ ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡- 0949910908 (0923747044) 0934370254 /0914344306/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል
