Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም የፈርኒቸር እቃዎች፣ ጽዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ልዩ ልዩ ህትመቶች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ የሆኑ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም የፈርኒቸር እቃዎች፣ ጽዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ልዩ ልዩ ህትመቶች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ የሆኑ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል በመሆኑም፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው።
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  5. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤ በእያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ ከሥራ ዘርፉ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግልፅ የሚነበብ ማህተም መምታት አለባቸው።
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  8. መስሪያ ቤቱ የጨረታውን ዋጋ በጥቅል ወይም በተናጠል ሊያወዳድር ይችላል።
  9. በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሰው የዕቃ ወይም አገልግሎት ብዛት ውል ከመፈረሙ በፊት እንደ በጀቱ ከፍ ወይም ዝቅ ሊል ይችላል፤ ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ 50 ብር (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ከቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / Bid Bond / ለእቃው የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በውስጥ ገቢ ካርኒ አስገብቶ ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  11. ተጫራቾች በቀረበው ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ፍ/ቤት የግዥ /ፋ/ን/አስ /ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11:20 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ይታሸጋል። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሀሳቦች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል፤ የቫት ተመዝጋቢዎች ዝቅ ብለው ሲወዳደሩ ሰነዳቸው የተሟላ መሆን አለበት።
  13. የጨረታው መክፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09-10-47-38-19/ 011-13-20-004 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. በማንኛውም ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ለአገልግሎት ከብር 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር) በላይ የቅድመ ግብር ታክስ ሶስት ፐርሰንት ተቀንሶ ለመንግሥት ይከፈላል።
  17. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻ እና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መምታት አለባቸው።
  18. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ይወረሳል፤ በመንግሥት ጨረታ ላይ ለሁለት አመት እንዳይወዳደሩ ይደረጋል፡፡
  19. ስርዝ ድልዝ፤ ፍቀት ያለው ፍሉድ የነካው ሰነድ ተቀባይነት የለውም በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት

 

Save Tender